Copy
Facebook
Twitter
LinkedIn
YouTube
Website
Flickr
Email

ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች፡ ዘንድሮ በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ሰዎች እና አካባቢዎች የሚሰጠው ትኩረት እና ምላሽ አሁንም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ነው

የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብቶች ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ ማድረግ ይኖርባቸዋል

ሪፖርቱን ያንብቡ
In a first of its kind Human Rights Situation Report on Ethiopia EHRC submitted to the House of Peoples’ Representatives the Commission call for government to protect, respect and guarantee human rights at all times

The report covers the period between June 2021 and June 2022 (Ethiopian fiscal year) and consists of an overall assessment of the human rights situation in the country; key positive developments, main concerns, challenges and recommendations
 
READ THE REPORT
Consultative meeting on monitoring and implementing the recommendations of United Nations human rights treaty bodies and the Universal Periodic Review

Coordination of efforts among stakeholders is necessary to ensure effective implementation of treaty body and UPR recommendations

READ MORE

 
በኢትዮጵያ ነፃነታቸውን አላግባብ እና በዘፈቀደ የተነፈጉ ሰዎች መብቶች ላይ ያተኮረው የመጀመሪያው ብሔራዊ ሕዝባዊ ምርመራ (National Public Inquiry) በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

ብሔራዊ ምርመራ ውስብስብና ተደጋጋሚ የሆኑ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በበርካታ አካባቢዎች የሚታዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በጥልቀት ለመመርመር እና ስልታዊና ዘርፈ ብዙ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ የሚጠቅም ዘዴ ነው

ተጨማሪ እወቅ


 
ለፖሊስ፣ ለመንግሥት አገልግሎት ሰጪ አካላት፣ ለተለያዩ ሲቪክ ማኅበራት እና ለወጣቶች በኢሰመኮ የተሰጡ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ስልጠናዎች

ስልጠናዎቹ መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን በተለይም ሰብአዊ ክብር፣ እኩልነት፣ ነፃነት፣ አድሎ አለመፈጸም እና ኃላፊነት የመሳሰሉት የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን በተለያዩ አሠራሮች፣ ሂደቶች እና እቅዶች ጋር ስላላቸው ግንኙነት የተመለከቱ ነበሩ
 
ተጨማሪ ያንብቡ
በኢሰመኮ የክልል ከተሞች ጽሕፈት ቤቶች በሰኔ ወር ከተካሄዱ ዝግጅቶች በጥቂቱ

የተከበሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጉብኝት፣ ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ቀን ስለማሰብ፣ የማረሚያ ቤት ክትትል ሥራ ግኝቶችን ለባለድርሻ አካላት ማጋራት
 
ተጨማሪ ያንብቡ
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፡እየተበራከቱ የመጡ ከአስተዳደራዊ መዋቅር እና ከድንበር መካለል ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች መንስዔነት የሚያገረሹ ግጭቶች ዘላቂ ምላሽ ይሻል

በግጭቶች የተጎዱ ሰዎችና አካባቢዎችንም መልሶ ለመጠገን እና ለማቋቋም በቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋል
 

ኢሰመኮ በክልሉ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከሁሉም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክልል እና የፌዴራል መንግሥት አካላት ጋር የሚያደርገውን ምክክር እና ክትትል ይቀጥላል

ተጨማሪ ያንብቡ
ኢሰመኮ በፖሊስ ማቆያዎች እና በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በጥበቃ ስር ያሉ ተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባደረገው ክትትል የተገኙ ግኝቶችና ምክረ-ሃሳቦች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረጉ ውይይቶች

ተሳታፊዎቹ ኮሚሽኑ ክትትል ሥራውን ማካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉት ገልጸው በክትትሉ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን በመፍታት ረገድ ለሚመለከታቸው አካላት የውትወታ ሥራ በመስራት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል

ተጨማሪ ለማወቅ

 
ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ በአማራ ክልልና በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ባደረገው ክትትል የተገኙ ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄዱ የምክክር መድረኮች

አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች በግጭቱ የደረሰባቸውን ከፍተኛ የመብቶች ጥሰት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

ተጨማሪ ያንብቡ

 
የሚድያ ሠራተኞችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሕግ አግባብ ውጪ እና ያሉበት ቦታ ሳይገለጽ የታሰሩ ሰዎችን በተመለከተ

የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ አካላት በአፋጣኝ የተያዙ ሰዎች የሚገኙበትን ቦታ እንዲገልጹና ተዓማኒ ክስ የማይቀርብ ከሆነ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ እንዲያደርጉ ኢሰመኮ በአጽንዖት ያሳስባል
 
ተጨማሪ ለማወቅ
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፡ በፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ የተጠርጣሪ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ በተደረገ ክትትል ውጤት እና ምክረ-ሃሳቦች አፈጻጸም ዙሪያ ከፍትሕ አካላት ጋር የተደረገ ውይይት

የፍትሕ አካላት በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን መብቶች ከማክበር፣ ከማስከበርና ከማስጠበቅ አኳያ ቀዳሚ ባለግዴታዎች ናቸው
ተጨማሪ ያንብቡ
Kellem Wollega Zone- Oromia Region: EHRC Calls for an Urgent Reinforcement of Government Security Forces

The continued insecurity in the area and what appears to be the ethnically targeted killing of residents must be put to a stop immediately
FIND OUT MORE
EHRC ON SOCIAL MEDIA
EHRC ON THE NEWS
ሶማሌ እና ኦሮምያ ክልል አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠታቸው ድርቁ መባባሱን ኢሰመኮ ገለፀ – ቪኦኤ አማር

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን እና በሱማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ የክልሎቹ እና የፌዴራል መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠታቸው ጉዳት መድርሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
 
ተጨማሪ ያንብቡ
EHRC on the News
ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established as per the Federal Constitution and reporting to House of People’s Representatives as a national human rights institution with the mandate for promotion and protection of human rights. (Article 55/14 of FDRE Constitution cum Proclamation No. 210/2000, as amended by Proclamation No. 1224/2020)
#KeepWordSafe
#HumanRightsForAll
Share Share
Tweet Tweet
Share Share
Forward Forward
Copyright © 2022 Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), All rights reserved.


Want to change how you receive these emails?
You can update your preferences or unsubscribe from this list.

Email Marketing Powered by Mailchimp