Copy
Facebook
Twitter
LinkedIn
YouTube
Website
Flickr
Email

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሰመራና አጋቲና ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች በአፋጣኝና ያለቅድመ ሁኔታ ሊለቀቁ ይገባል

በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል፤ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸውም እስኪመለሱ ድረስ በካምፑ ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ በሙሉ ፈቃደኝነትና ያለ ማናቸውም ዓይነት የእንቅስቃሴ ገደብ ሊሆን ይገባል

ተጨማሪ ያንብቡ
ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ረቂቅ የግብረገብ ትምህርት ከሪኩለም (መማሪያ) ውስጥ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ማስረጽ ስለማስቻል

የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እራሱ ሰብአዊ መብት እንደመሆኑ ሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ ትምህርት በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የማድረግ ጥረት የአትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገር አቀፍ ደረጃ ከገባው ግዴታ ጋር የሚያያዝ ነው

ተጨማሪ እወቅ

 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ላይ የሲቪል ማኅበራት ሚና ማጎልበት

የምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን የመከታተልና ሪፖርት የማቅረብ ተቀዳሚ ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም ሲቪል ማኅበራት ይህንን አስመልክቶ የራሳቸውን ምልከታ ሪፖርት ለማቅረብ ልዩ ዕድል አላቸው

ተጨማሪ እወቅ

 
የማሰቃየት ተግባር ሰለባ ከሆኑ ተጎጂዎች ጎን የመቆም ዓለም አቀፍ ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀ አውደ ጥናት

በአጠቃላይ አውደ ጥናቱ አስተማሪ እና ወቅታዊ የሆኑ ሀሳቦችን በፈጠራ ሥራዎች በታገዘ መልኩ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሻለ የአሠራር ስልት ለመፍጠር እንዲያስችል እና የመፍትሔ ሃሳቦችን ላይ ለመወያየት አስችሏል

🎥 የማሰቃየት ተግባር ሰለባ የሆኑ ተጎጂዎችን የሚደርስባቸውን አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት የሚያሳይ አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል (ፊልም)
 
ተጨማሪ ያንብቡ
በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ተፈጽሟል የሚባል ወንጀል እና ቅድመ ክስ እስር

በሚድያ አዋጁ አንቀጽ 86(1) የተመለከተው የቅድመ እስር ክልከላ ከአዋጁ አንቀጽ 3(1) እና 6(3) ጋርም ተቀናጅቶ ሲነበብ ለተመዘገበ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ዓይነት ሚዲያዎች የተቀመጠ የሕግ ጥበቃ መሆኑን የሚያመለክት ነው
 
ማብራሪያውን ያንብቡ
በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመዘዋወር ላይ የሚገኘውን በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ በማድረግ በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል በተመለከተ

ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በድጋሚ ያሳስባል
 
ተጨማሪ ያንብቡ
ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጥቃት

መንግሥት በሲቪል ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ፣ በማንኛውም ሁኔታ ሲቪል ሰዎች የጥቃት ዒላማ እንዳይደረጉ ተገቢ የሆነ ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያደርግ፣ እንዲሁም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ
 
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግሥት የስደተኞችን የደኅንነት መብት መከበሩን በሚያረጋግጥበት ሂደት ለልዩ ፍላጎት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል

የስደተኛ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ፍላጎቶቻቸውን መሰረት ያደረገ እገዛ አስፈላጊ ነው

ተጨማሪ ለማወቅ

 
በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ድርጊቶችን ለማስወገድ የተቀናጀ ጥረት ሊደረግ ይገባል

የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሕፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጥና ትምህርት ማቋረጥን ጨምሮ፣ ለጾታዊ ጥቃት፥ ለጉልበት እና ለወሲባዊ፥ ብዝበዛ፣ ለልመና እና ለሌሎች ጎጂ ድርጊቶች ተጋላጭ ናቸው

ተጨማሪ ያንብቡ

 
ጋምቤላ ክልል፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች

የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ መቆጠብ እና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
 
ተጨማሪ ለማወቅ
የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ሰብአዊ መብቶች መከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል

ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም
ተጨማሪ ያንብቡ
የአካል ጉዳተኞች ሥራ የማግኘት መብት እንዲከበር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል

የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብትን የሚመለከት አዋጅ የወጣ እና ሥራ ላይ የዋለ ቢሆንም፤ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ያለው ያልተጣጣመ አሠራር አካል ጉዳተኞች በሥራ ቅጥር፣ ዕድገት፣ ድልድል፣ ዝውውር፣ ሥልጠናና ሌሎች የሥራ ሁኔታዎች ወቅት መድልዎ እንዲደርስባቸው መንስኤ ነው

ተጨማሪ ለማወቅ

 
Strengthening the Role of Civil Society Organizations in the United Nations Universal Periodic Review

While the State has the primary responsibility to report on the implementation of recommendations, CSOs are uniquely placed to report on their observations on implementation

READ MORE

 
ልዩ ትኩረት በአረጋውያን ላይ ለሚደርስ ጥቃት እና ጉዳት

በአረጋውያን ላይ የሚደርሰውን ማኅበራዊ መገለል እና አድልዎ ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና እና የባህል መብቶች ጥሰት ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ እና ሰብአዊ መብቶቻቸው ሊጠበቁ፣ ሊከበሩ እና ሊሟሉ ይገባል
መግለጫውን ያንብቡ
EHRC Visited Ethiopian Migrants held in Wajir County, Kenya

Female migrants told of a vicious circle of irregular migration where their human rights are put at risk as they continue to fall prey to smugglers and corrupted authorities
LEARN MORE
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች እና ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ

የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበርን በሚመለከት በኢሰመኮ የተደረገ የክትትል ሥራ የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን የማግኘት፣ የእኩልነትና ከአድልዎ ነፃ የመሆን እንዲሁም የሥራ ዋስትና የማግኘት መብቶች እየተጣሱ እንደሆነ ማመላከቱ ተገልጾ በምክረ ሃሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰብስቧል

ተጨማሪ ለማወቅ

 
Regional Meeting on the Establishment of an Alert and Reporting Mechanism on Torture and other Ill-treatment to the African Commission on Human and Peoples’ Rights (ACHPR)

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) participated in the Regional Meeting on the Establishment of an Alert and Reporting Mechanism on Torture and other Ill-treatment to the African Commission on Human and Peoples’ Rights (ACHPR) held from 27- 29 May, 2022, in Abidjan, Côte d’Ivoire.

READ MORE

 
An art exhibition themed displacement, migration and refugee status took place on the margins of a high level consultation to mark #WorldRefugeeDay
FIND OUT MORE
EHRC ON SOCIAL MEDIA
LEARN ABOUT HUMAN RIGHTS
የዋስትና መብት | The Right to Bail
EHRC ON THE NEWS
At least 200 civilians killed in western Ethiopia, say reports and officials – CNN

The attack on the town of Gimbi was connected to fighting between government forces and the OLA, according to a statement from the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). The EHRC told CNN Monday that the assault has left “scores of people injured, villages destroyed, and entire communities traumatized.”

READ MORE

 
ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የመንግሥት ኃይሎች ጭምር መሳተፋቸውን ኢሰመኮ ገለፀ – VOA Amharic: ቪኦኤ አማርኛ

አቶ ይበቃል ግዛው፣ ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 11 በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ደግሞ፣ በጥቃቱ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል

ለበለጠ መረጃ

 
EHRC on the News
ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established as per the Federal Constitution and reporting to House of People’s Representatives as a national human rights institution with the mandate for promotion and protection of human rights. (Article 55/14 of FDRE Constitution cum Proclamation No. 210/2000, as amended by Proclamation No. 1224/2020)
#KeepWordSafe
#HumanRightsForAll
Share Share
Tweet Tweet
Share Share
Forward Forward
Copyright © 2022 Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), All rights reserved.


Want to change how you receive these emails?
You can update your preferences or unsubscribe from this list.

Email Marketing Powered by Mailchimp